አብያተክርስቲያናትን ለመትከል ደቀ-መዛሙርትን ማብዛት

የግሎባል ዲሳይፕል (የደቀ-መዝሙርነት-ተልዕኮ) ሥልጠና ግብ ሌሎችን የክርስቶስ ደቀ-መዛሙርት የሚያደርጉ አገልጋዮችን በማስታጠቅ መላክና በብዛት ወንጌል ባልደረሳቸው ህዝቦች መሃል አዳዲስ የአማኞችን ህብረት ማባዛት ነው፡፡

ትኩረታችን የደቀ-መዝሙርነት-ተልዕኮ የሥልጠና መርሃ-ግብር ከፍታችሁ ደቀ-መዛሙርትን የሚያፈሩትን በማሰልጠን ሄደው አዳዲስ ደቀ-መዛሙርትን እንዲያባዙና አብያተ ክርስቲያናትን እንዲተክሉ መርዳት ነው፡፡ የግሎባል ዲሳይፕል ሥልጠና መርሃ ግብር ሰልጣኞች በባህሪያቸው ክርስቶስን እንዲመስሉና የኢየሱስ አምባሳደር በመሆን ሌሎችን የክርስቶስ ደቀ-መዝሙር በማድረግ ዓለምን በወንጌል እንዲደርሱ ማሰልጠን ነው፡፡ ይህ ሥልጠና ሰልጣኞች እግዚአብሔር ለዓለም ያለውን ዓላማ እንዲገነዘቡ በማድረግ በክርስቶስ ተልዕኮ ውስጥ አጋር ሰራተኞች እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡ የዚህ ሥልጠና መርሃ ግብር-ዓላማ መንፈሳዊ ግንኙነትን ማጎልበት፣ የፀሎት ህይወትን ማሳደግ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ምስክርነትንና አገልግሎትን ሁሉ ያካተተ ነው፡፡

የግሎባል ዲሳይፕል የሥልጠና መርሃ-ግብር ሰልጣኞች ከ2 ሳምንት እስከ 4 ወራት ለሚደርስ ጊዜ በሙሉ ጊዜ ሥልጠና መስጠት ነው፡፡ ይህንን ሥልጠና ተከትሎ ሰልጣኞች ቢያንስ ከ 4 ሳምንታት እስከ 11 ወራት የሚቆይ የሙሉ ጊዜ የመስክ የወንጌል ስርጭት ያካሄዳሉ፡፡ የመስክ የወንጌል ሥርጭቱን ተከትሎ ከ2 እስከ 3 ቀን የሚቆይ የመስክ አገልግሎት ምዘና ጊዜ እንዲኖራቸውም ይጠበቃል፡፡

የግሎባል ዲሳይፕል ስልጠና መርሃ-ግብር እስከ አንድ ዓመት ለሚደርስ ጊዜ ሊካሄድ ይችላል፡፡

ማንኛውም የግሎባል ዲሳይፕልስ አሊያንስ አካል መሆን የሚፈልግ የደቀ-መዝሙርነት-ተልዕኮ የሥልጠና ፕሮግራም ቢያንስ በሦስት አጥቢያ ቤተ-ክርስቲያናት (ማህበረ-ምዕመናን) ጥምረት ሥር ሆኖ የሚመራ ሊሆን ይገባዋል፡፡

ስለዚህ ጥምር ቤተ-ክርስቲያናቱ መርሃ-ግብሩ በአካባቢው ቀጣይነቱ አስተማማኝ እንዲሆንና እየተባዛ እንዲሄድ የሚያስችል የአመራር ቡድን ያደራጃሉ፡፡ መርሃ-ግብሩን የሚያንቀሳቅሱት ጥምር ቤተ-ክርስቲያናትን የበጀት አቅርቦት መሰረት ያደረገ መጠነኛ የዘር ገንዘብ ድጋፍም ከግሎባል ዲሳይፕልስ አሊያንስ ይደረግላቸዋል፡፡ ይህን ጉዳይ በተመለከተ የበለጠ ለመረዳት የአሊያንሱን አስተባባሪዎች (ፋስልተተሮች) ማነጋገርና የግሎባል ዲሳይፕልን (ደቀ-መዛሙርት-ተልዕኮ) መጽሔት መጠየቅ ትችላላችሁ፡፡

በግሎባል ዲሳይፕል ሥልጠና መርሃ-ግብር አብረን በመሥራት፣ በመማማር' አብረን በመፀለይ፣ ዕውቀትንና፣ ያለንን ሃብት በጋራ በመጠቀም ባጠቃላይ የመርሃ-ግብራችሁን ውጤታማነት መጨመር እንችላለን፡፡

እንዲሁም የእናንተን አዲስ የደቀ-መዝሙርነት-ተልዕኮ መርሃ-ግብር ከሌሎች በዓለም ዙሪያ እየሰሩ ካሉ የግሎባል ዲሳይፕል ሥልጠና መርሃ-ግብሮች ጋር በማገናኘት የምትደጋገፉበትንና የምትበረታቱበትን መንገድ

የደቀመ ዝሙ ርነትናሚ ሲዮናዊ ተልዕኮ

Contact us

Global Disciples, Ethiopia

P.O.BOX Addis Ababa, 17202

TELE: (251) 9-30100568(67)

         (251) 930077391

Understanding Global Disciples

Do you want to become a better leader, one who reflects Jesus Christ in the work you do or your role in ministry? Are you looking for men and women who can be effective leaders in your church, denomination or business? Does your church or organization see the need to train and mentor those who can become the influential leaders of the next generation? Are you looking for ways to raise up leaders for newly-planted churches? If so, the LEAD track of Global Disciples offers you an effective model for training Christ-like leaders in your local context.

JoomShaper