አብያተ ክርስቲያናትን ለመ ትከል ክርስቶስን የሚ መ ስሉ መ ሪዎች ማ ብ ዛት

በማደግ ላይ የምትገኝ ቤተክርስቲያን የሚያድጉ መሪዎችን ትፈልጋለች፡፡ ውጤታማ አመራርን ማጎልበት እያንዳንዷ ቤተ-ክርስቲያን ታላቁን ተልዕኮ እንድትፈፅም ለማስታጠቅ መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ በግሎባል ሊድ አማካይነት ቤተ-ክርስቲያኖቻችሁ ውጤታማነቱ የተመሰከረለት ክርስቶስን የሚመስሉ በሺህዎች የሚቆጠሩ መሪዎችን በየአጥቢያው ማጎልበት እንዲችሉ አርአያነት ያለው ሥልጠና መስጠት ትችላላችሁ፡፡

ግሎባል ሊድ አብያተ-ክርስቲያናት ሆን ብለው አስበውበት' ስልታዊ በሆነ ዕቅድ መሪዎችን ከሥራቸው ሳይፈናቀሉ በአነስተኛ ወጪ ማሰልጠን የሚችሉበትን አርአያነት ያለውን አዕምሮን ብቻ በዕውቀት ከመሙላት ይልቅ በህይወት ለዋጭነት ላይ ትኩረት አድርገው እንዲያስታጥቋቸው ጥሪ ያቀርባል፡፡

ማናቸውም አቢያተ-ክርስቲያናት መርሃ-ግብራቸው የግሎባል ዲሳይፕልስ አሊያንስ አባል እንዲሆን ከፈለጉ ሊጠቀሙባቸው የሚችሉትን 22 መሠረታዊ ትምህርቶችን የያዘ ሥርዓተ-ትምህርት ተቀርፆ ቀርቧል፡፡ አጥቢያ ቤተ-ክርስቲያኖቻችሁ የራሳቸውን አሰልጣኞችና ሰልጣኞችን መልምለው ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የዚህ የአመራር ሥልጠና ወጪም እጅግ ዝቅተኛ በመሆኑ አብዛኛውን ጊዜ በተሳታፊዎቹ በራሳቸው የሚሸፈን ነው፡፡

 

ግሎባል ሊድ አብያተ-ክርስቲያናት የአመራር ሥልጠና መርሃ-ግብራቸውን እንዲመሩ የመረጡትን መሪዎችን ያሠለጥናል፣ ይህም ስልጠና ቢያንስ 4½ ቀናትን የሚፈጅ ሲሆን የመርሃ-ግብሩን መሪዎች ብቃት የሚያጠናክር ጥልቀት ያለው ሥልጠና ነው፡፡ በስልጠናውም ወቅት የእያንዳንዱ አመራር ሥልጠና መርሃ-ግብር መሪም አውዳዊ የሆነውን የአመራር ሥልጠና መርሃ-ግብሩን ዕቅድ ያዘጋጃል፡፡ ይህም የሥልጠና ዕቅድ በሣምንት አንድ ምሽት ወይም በወር አንድ ሙሉ ቀን በመገናኘት ቢያንስ ለስድስት ወራት የሚቆይ ሊሆን ይገባል፡፡

በሥልጠናውም መጨረሻ እነዚህ የየመርሃ-ግብሩ መሪዎች ወደ ላኩአቸው አብያተ-ክርስቲያኖቻቸው ተመልሰው አዳዲስ መሪዎችን በሶስት ዋና ዋና አቅጣጫዎች ማለትም በባህሪይ፣ በእውቀትና በክህሎት ለማጐልበት ብቃት ያገኛሉ፡፡

እንደዚህ ያሉ የአመራር መርሃ-ግብሮች በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሺህዎች የሚቆጠሩ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎችን ባህሪይና አመለካከት በመለወጥ ውጤታማ በመሆን ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ ስልጠና ክርስቶስን የሚመስሉ መሪዎችን ማብዛት ብቻ ሳይሆን የስልጠናው መርሃ-ግብሮች ራሳቸው ቤተ-ክርስቲያን በተመሠረተችባቸው አዳዲስ ሥፍራዎች ሁሉ በፍጥነት እንዲባዙ ያስችላቸዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ የክርስቶስ አካል ወንጌል ባልደረሳቸው አካባቢዎች እድገቷና መስፋፋቷ እንዲቀጥል ጠንካራ መሠረትን ጥሏል፡፡

 

Contact us

Global Disciples, Ethiopia

P.O.BOX Addis Ababa, 17202

TELE: (251) 9-30100568(67)

         (251) 930077391

Understanding Global Disciples

Do you want to become a better leader, one who reflects Jesus Christ in the work you do or your role in ministry? Are you looking for men and women who can be effective leaders in your church, denomination or business? Does your church or organization see the need to train and mentor those who can become the influential leaders of the next generation? Are you looking for ways to raise up leaders for newly-planted churches? If so, the LEAD track of Global Disciples offers you an effective model for training Christ-like leaders in your local context.

JoomShaper